am_obs/content/21.md

7.3 KiB

21. እግዚአብሔር መሲሑን ተስፋ ሰጠ

OBS Image

ገና ከመጀመሪያው፣ እግዚአብሔር መሲሑንለመላክ ዐቀደ። የመጀመሪያው የመሲሑ ተስፋ ወደ አዳምና ሔዋን መጣ። እግዚአብሔርየእባቡን ራስ የሚቀጠቅጥ የሔዋን ዘር እንደሚወለድ ተስፋ ሰጠ። ሔዋንን ያታለለው እባብ ሰይጣን ነበር። ተስፋው መሲሑ ሰይጣንን ፍጹም ያሸንፈዋል ማለት ነው።

OBS Image

በእርሱ በኩል የዓለም ሕዝብ ወገኖች በሙሉ በረከት እንደሚቀበሉ እግዚአብሔር ለአብርሃም ተስፋ ሰጠው። ይህ በረከት ወደ ፊት መሲሑ ሲመጣ ይፈጸማል። እርሱ በዓለም ካሉ ከሁሉም የሕዝብ ወገኖች የሆኑ ሕዝቦች እንዲድኑ ያደርጋል።

OBS Image

ወደ ፊት እንደ ሙሴ ያለ ሌላ ነቢይ እንደሚያስነሣ እግዚአብሔር ለሙሴ ተስፋ ሰጠው። ይህ ቆይቶ ስለሚመጣው መሲሕ የተሰጠ ሌላ ተስፋ ነበር።

OBS Image

ከዝርያዎቹ አንዱ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ንጉሥ ሆኖ ለዘላለም እንደሚገዛ እግዚአብሔር ለንጉሥ ዳዊት ተስፋ ሰጠው። ይህም መሲሑ ከዳዊት ዝርያዎች አንዱ ይሆናል ማለት ነበር።

OBS Image

እግዚአብሔር ዐዲስ ቃል ኪዳን እንደሚያደርግ በነቢዩ ኤርምያስ በኩል ተስፋ ሰጠ፣ ይህ ቃል ኪዳን እግዚአብሔር በሲና ከእስራኤል ጋር እንዳደረገው ቃል ኪዳን ግን አይደለም። በዐዲሱ ቃል ኪዳን እግዚአብሔር ሕጉን በሕዝቡ ልብ ይጽፋል፣ ሕዝቡ በግል እግዚአብሔርን ያውቁታል፣ ሕዝቡ ይሆናሉ፣ እግዚአብሔር ኃጢአታቸውን ይቅር ይላል። መሲሑ ዐዲሱን ኪዳን ይጀምራል።

OBS Image

ደግሞም የእግዚአብሔር ነቢያት መሲሑ ነቢይ፣ ካህን እንዲሁም ንጉሥ ይሆናል አሉ። ነቢይ የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ ከዚያም የእግዚአብሔርን ቃል ለሕዝቡ የሚያውጅ ሰው ነው። እግዚአብሔር ለመላክ ተስፋ የሰጠው መሲሕ ፍጹም ነቢይ ይሆናል።

OBS Image

እስራኤላውያን ካህናት ስለ ኃጢአታቸው በሚደርስባቸው ቅጣት ምትክ በሕዝቡ ፈንታ ለእግዚአብሔር መሥዋዕቶችን አቀረቡ። ደግሞም ካህናት ስለ ሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ። መሲሑ ፍጹም መሥዋዕት አድርጎ ራሱን ለእግዚአብሔር የሚያቀርብ ፍጹም ሊቀ ካህናት ይሆናል።

OBS Image

ንጉሥ በመንግሥቱ ላይ የሚገዛና በሕዝቡ ላይ የሚፈርድ ሰው ነው። መሲሑ በቅድማያቱ በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ፍጹም ንጉሥ ይሆናል። በመላው ዓለም ላይ ለዘላለም ይገዛል፣ እንዲሁም ሁልጊዜ በቅንነት ይፈርድና ትክክለኛ ውሳኔ ይሰጣል።

OBS Image

የእግዚአብሔር ነቢያት ስለ መሲሑ ሌሎች ብዙ ነገሮችን ተንብየዋል። ነቢዩ ሚልክያስ መሲሑ ከመምጣቱ በፊት ታላቅ ነቢይ እንደሚመጣ አስቀድሞ ተነበየ። መሲሑ ከአንዲት ድንግል እንደሚወለድ ነቢዩ ኢሳይያስ ተነበየ። ነቢዩ ሚክያስ መሲሑ በቤተ ልሔም ከተማ ይወለዳል አለ።

OBS Image

ነቢዩ ኢሳይያስ መሲሑ በገሊላ ይኖራል፣ ልባቸው የተሰበረ ሰዎችን ያጽናናል፣ እንዲሁም ለተማረኩት ነጻነትንና ለታሰሩት መፈታትን ያውጃል። ደግሞም ነቢዩ መሲሑ የታመሙና መስማት፣ ማየት፣ መናገር፣ ወይም መራመድ የማይችሉትን ሕዝብ እንደሚፈውስ ተነበየ።

OBS Image

ደግሞም ነቢዩ ኢሳይያስ መሲሑ ያለ ምክንያት እንደሚጠላና ተቃውሞ እንደሚደርስበት ተነበየ። ሌሎች ነቢያት መሲሑን የገደሉት እነዚያ በልብሶቹ ላይ ዕጣ እንደሚጣጣሉና ወዳጁ እንደሚክደው አስቀድመው ተነበዩ። ነቢዩ ዘካርያስ መሲሑን ለሚክደው ወዳጅ ሠላሳ ብር እንደሚከፍሉት ተነበየ።

OBS Image

ደግሞም ነቢዩ ስለ መሲሑ አሟሟት ተናገረ። ኢሳይያስ ሰዎች መሲሑን እንደሚተፉበት፣ እንደሚያፌዙበትና እንደሚመቱት ተነበየ። ምንም ስሕተት ነገር ያላደረገ ቢሆንም እንኳ ይወጉታል በታላቅ ሕመምና ሥቃይ ይሞታል።

OBS Image

ደግሞም ነቢያት መሲሑ ኃጢአት የሌለበት ፍጹም ይሆናል አሉ። የሌሎች ሰዎችን ኃጢአት ቅጣት ለመቀበል እርሱ ሞተ። የእርሱ መቀጣት በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል ሰላምን ያመጣል። በዚህ ምክንያት መሲሑን ማድቀቅ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር።

OBS Image

መሲሑ እንደሚሞትና እግዚአብሔር ደግሞ ከሙታን እንደሚያስነሣው ነቢያት አስቀድመው ተነበዩ። እግዚአብሔር በመሲሑ ሞትና ትንሣኤ በኩል ኃጢአተኞችን ለማዳን ዕቅዱን ይፈጽምና ዐዲሱን ኪዳን ይጀምራል።

OBS Image

እግዚአብሔር ለነቢያት ስለ መሲሑ ብዙ ነገሮችን ገለጠላቸው፣ ነገር ግን መሲሑ ከእነዚያ ነቢያት በአንዳቸውም ጊዜ አልመጣም። ከእነዚህ ትንቢቶች የመጨረሻው ከተተነበየ ከ400 ዓመታት በኋላ፣ ልክ በትክክለኛው ጊዜ፣ እግዚአብሔር መሲሑን ወደ ዓለም ይልካል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘፍጥረት 3፡15፤ 12፡1-3፤ ዘዳግም 18፡15፤ 2ኛ ሳሙኤል 7፤ ኤርምያስ 31፤ ኢሳይያስ 59፡16፤ ዳንኤል 7፤ ሚልክያስ 4፡5፤ ኢሳይያስ 7፡14፤ ሚክያስ 5፡2፤ ኢሳይያስ 9፡1-7፤ 35፡3-5፤ 61፡53፤ መዝሙር 22፡18፤ 35፡19፤ 69፡4፤ 41፡9፤ ዘካርያስ 11፡12-13፤ ኢሳይያስ 50፡6፤ መዝሙር 16፡10-11።