am_obs/content/11.md

2.8 KiB

11. ፋሲካ

OBS Image

እስራኤላውያንን ካልለቀቀ የሰዎችንና የእንስሳትን ተባዕት በኵር ሁሉ እንደሚገድል እግዚአብሔር ፈርዖንን አስጠነቀቀው። ፈርዖን ይህን በሰማ ጊዜ፣ አሁንም ማመንና ለእግዚአብሔር መታዘዝ እምቢ አለ።

OBS Image

እግዚአብሔር በእርሱ ያመነ የማንኛውም ሰው በኵር ወንድ ልጅ ለማዳን መንገድ አዘጋጀ። እያንዳንዱ ቤተ ሰብ ፍጹም የሆነ ጠቦት መርጦ አረደ።

OBS Image

እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን የጠቦቱን ደም በቤታቸው በር ላይ እንዲቀቡት፣ ሥጋውንም ጠብሰው ያለ እርሾ ከተጋገረው ቂጣ ጋር በፍጥነት እንዲበሉት ነገራቸው። ደግሞ በበሉት ጊዜ ከግብፅ ለመውጣት እንዲዘጋጁ ነገራቸው።

OBS Image

እስራኤላውያን ልክ እግዚአብሔር እንዲያደርጉ እንዳዘዛቸው ሁሉንም ነገር አደረጉ። እኩለ ሌሊት ላይ እግዚአብሔር በመላው ግብፅ አልፎ ወንድ በኵርን ሁሉ ገደለ።

OBS Image

የእስራኤላውያን ቤቶች ሁሉ በሮቻቸው ደም ተቀብተው ነበር፣ ስለዚህ እግዚአብሔር በቤቶቹ አለፈ። በቤቶቹ ውስጥ የነበረው ሰው ሁሉ ዳነ። እስራኤላውያን በጠቦቱ ደም ምክንያት ዳኑ።

OBS Image

ግብፃውያን ግን በእግዚአብሔር አላመኑም፣ ትእዛዛቱንም አልፈጸሙም። ስለዚህ እግዚአብሔር በቤቶቻቸው አላለፈም። እግዚአብሔር የግብፃውያንን በኵር ወንዶችን ሁሉ ገደለ።

OBS Image

በእስር ቤት ካለው በኵር እስረኛ ጀምሮ እስከ ፈርዖን በኵር ድረስ እያንዳንዱ ግብፃዊ በኵር ወንድ ሞተ። ከጥልቅ ሐዘናቸው የተነሣ በግብፅ የነበሩ ብዙ ሰዎች ያለቅሱና ይጮኹ ነበር።

OBS Image

በዚያው ሌሊት ፈርዖን ሙሴንና አሮንን ጠርቶ፣ “እስራኤላውያንን ይዛችሁ አሁኑኑ ሂዱ!” አላቸው።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘጸአት 11፡1-12፡32።