am_obs/content/06.md

2.6 KiB

6. እግዚአብሔር ለይስሐቅ ሚስት አዘጋጀለት

OBS Image

አብርሃም በጣም ባረጀ ጊዜ ይስሐቅ ዕድሜው ለአቅመ አዳም ደረሰ። ስለዚህ አብርሃም ከአገልጋዮቹ አንዱን ወደ ዘመዶቹ ምድር ለልጁ ለይስሐቅ ሚስት እንዲያመጣለት ላከው።

OBS Image

የአብርሃም ዘመዶች ወደሚኖሩበት ምድር ከረጅም ጒዞ በኋላ ደረሰ። እግዚአብሔርም የተላከውን የአብርሃምን አገልጋይ ወደ ርብቃ መራው። ርብቃ የአብርሃም ወንድም የልጅ ልጅ ነበረች።

OBS Image

ርብቃ ቤተ ሰቦቿን ትታ ከአገልጋዩ ጋር ወደ ይስሐቅ ቤት ለመሄድ ተስማማች። እንደ ደረሰችም ይስሐቅ አገባት።

OBS Image

ከረጅም ጊዜበኋላ አብርሃምሞተና እግዚአብሔርከአብርሃም ጋርየገባው የተስፋ ቃል ኪዳን ሁሉ ወደ ይስሐቅተላለፈ። እግዚአብሔርለአብርሃም ሊቈጠር የማይችል ዘር እንደሚኖረው ተስፋ ሰጥቶት ነበር። ይሁን እንጂ የይስሐቅ ሚስት ርብቃ ልጆች ልትወልድ አልቻለችም።

OBS Image

ይስሐቅ ለርብቃ ጸለየላትና እግዚአብሔር መንታ ልጆችን እንድታረግዝ ፍቃዱ ሆነ። ሁለቱ ልጆች በርብቃ ማኅፀን ሳሉ እርስ በርሳቸው ይታገሉ ነበር። ርብቃም በማኅፀንዋ እየሆነ ያለው ምን እንደሆነ እግዚአብሔርን ጠየቀች።

OBS Image

እግዚአብሔርም ርብቃን አላት፣ “በማኅፀንሽ ካሉት ከሁለቱ ልጆች ሁለት ሕዝቦች ይወጣሉ እነርሱም እርስ በርሳቸው ይታገላሉ ታላቁም ታናሹን ያገለግላል” አላት።

OBS Image

የርብቃ ልጆች በተወለዱ ጊዜ ታላቁ ልጅ ቀይና ፀጉራም ሆኖ ወጣ ‘ኤሳው’ ሲሉትም ስም አወጡለት፤ ታናሹም ልጅ የኤሳውን ተረከዝ ይዞ ወጣ ስሙንም ‘ያዕቆብ’ ሲሉ አወጡለት።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘፍጥረት 24፡1-25፤ 26።