am_obs/content/34.md

3.7 KiB

34.ኢየሱስ ሌሎች ታሪኮችን አስተማረ

OBS Image

ኢየሱስ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ሌሎች ብዙ ታሪኮችን አስተማረ። ለምሳሌ፣ እንዲህ አለ፣ “የእግዚአብሔር መንግሥት ሰው በማሳው የዘራትን የሰናፍጭ ዘር ትመስላለች። እርስዋም ከሁሉ ዘር የምታንስ ነች።”

OBS Image

“ነገር ግን የሰናፍጭ ዘር ባደገች ጊዜ አዕዋፍ መጥተው እስኪሰፍሩ ድረስ በአትክልት ቦታ ካሉ ተክሎች ሁሉ ትበልጣለች።

OBS Image

ኢየሱስ ሌላ ታሪክ ተናገረ፣ “የእግዚአብሔር መንግሥት ሴት ወስዳ ሁሉ እስኪቦካ ድረስ ከዱቄት ጋር የለወሰችው እርሾ ትመስላለች።

OBS Image

“ደግሞ የእግዚአብሔር መንግሥት ሰው በእርሻ ውስጥ የሸሸገው መዝገብ ትመስላለች። ሌላ ሰው መዝገቡን አገኘውና እንደ ገና ቀበረው። በጣም በደስታ ተሞልቶ ነበርና ሄዶ ያለውን ነገር ሁሉ ሸጠና በገንዘቡ እርሻውን ገዛው።”

OBS Image

“ደግሞ የእግዚአብሔር መንግሥት ዋጋዋ እጅግ ውድ የሆነ ዕንቊ ትመስላለች። የዕንቊ ነጋዴ ባገኛት ጊዜ ያለውን ነገር ሁሉ ሸጠና ገዛት።”

OBS Image

ከዚያ በኋላ ኢየሱስ በራሳቸው መልካም ሥራ ለሚታመኑና ሌሎችን ለሚንቁ አንዳንድ ሰዎች ታሪክ ተናገረ። “ሁለት ሰዎች ሊጸልዩ ወደ ቤተ መቅደስ ሄዱ። አንዱ ቀረጥ ሰብሳቢ ሲሆን፣ ሌላው የሃይማኖት መሪ ነበር” አለ።

OBS Image

“የሃይማኖት መሪው እንዲህ ብሎ ጸለየ፣ ‘እግዚአብሔር ሆይ፣ እንደ ሌሎች ሰዎች ሁሉ፣ ቀማኞችና ዓመፀኞች አመንዝሮችም፣ እንደዚህ ቀረጥ ሰብሳቢ ስላልሆንኩ አመሰግንሃለሁ።”

OBS Image

“ለምሳሌ፣ እኔ በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ እጾማለሁ፣ ከማገኘውም ገንዘብና ንብረት ሁሉ ከዐሥር አንድ አወጣለሁ።’”

OBS Image

“ቀረጥ ሰብሳቢው ግን ከሃይማኖት መሪው ራቅ ብሎ ቆመ፣ ወደ ሰማይ እንኳ አልተመለከተም። በዚህ ፈንታ፣ ደረቱን በእጁ እየመታ፣ ‘እግዚአብሔር ሆይ፣ እኔ ኃጢአተኛ ስለ ሆንኩ እባክህን ማረኝ።’”

OBS Image

ከዚያ በኋላ ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ “እውነት እላችኋለሁ፣ እግዚአብሔር የቀረጥ ሰብሳቢውን ጸሎት ሰማና ጻድቅ ነህ አለው። የሃይማኖት መሪውን ጸሎት ግን አልወደደም። እግዚአብሔር ራሱን ከፍ የሚያደርገውን ሁሉ ያዋርዳል፣ ራሱን የሚያዋርደውን ግን ከፍ ያደርጋል።’

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 13፡31-33፣ 44-46፤ ማርቆስ 4፡30-32፤ ሉቃስ 13፡18-21፤ 18፡9-14።