am_obs/content/31.md

3.0 KiB

31. ኢየሱስ በውሃ ላይ ተራመደ

OBS Image

ከዚያም ኢየሱስ ሕዝቡን እያሰናበተ እያለ ጀልባ ውስጥ ገብተው እየቀዘፉ ወደ ማዶ እንዲሻገሩ ለደቀ መዛሙርቱ ነገራቸው። ኢየሱስ ሕዝቡን ካሰናበተ በኋላ ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ። በዚያ ኢየሱስ ብቻውን ነበር፣ እስከ እኩለ ሌሊትም ጸለየ።

OBS Image

በዚሁ ጊዜ፣ ደቀ መዛሙርቱ ጀልባቸውን እየቀዘፉ ነበር፣ በእኩለ ሌሊት የደረሱት ወደ ሐይቁ አጋማሽ ብቻ ነበር። ነፋሱ በእነርሱ ላይ በኃይል ይነፍስ ስለ ነበር የሚቀዝፉት በጣም በችግር ነበር።

OBS Image

በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መጸለዩን ጨረሰና ወደ ደቀ መዛሙርቱ ሄደ። በውሃው ላይ እየተራመደ ሐይቁን አቋርጦ ወደ ጀልባቸው ሄደ!

OBS Image

ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን ባዩ ጊዜ በጣም ፈሩ፣ ምክንያቱም ምትሐት ያዩ መሰላቸው፣ ኢየሱስ የፈሩ መሆናቸውን ዐወቀ፣ ስለዚህ ወደ እነርሱ ተጣራና፣ “አትፍሩ። እኔ ነኝ!” አላቸው።

OBS Image

በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ኢየሱስን፣ “መምህር ሆይ፣ አንተስ ከሆንክ በውሃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዝ” አለው። ኢየሱስ ጴጥሮስን፣ “ና!” አለው።

OBS Image

ስለዚህ ጴጥሮስ ከጀልባው ወጣና በውሃው ላይ ወደ ኢየሱስ መራመድ ጀመረ። ነገር ግን አጭር ርቀት ከተራመደ በኋላ ዓይኖቹን ከኢየሱስ አዞረና ማዕበሉን ያይ ብርቱው ነፋስም ይሰማው ጀመር።

OBS Image

በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ፈራና በውሃው መስጠም ጀመረ። “መምህር ሆይ፣ አድነኝ!” ብሎ ጮኸ። ኢየሱስ ወዲያው እጆቹን ዘረጋና ያዘው። ከዚያም ጴጥሮስን፣ “አንተ እምነት የጎደለህ፣ ለምን ተጠራጠርህ?” አለው።

OBS Image

ጴጥሮስና ኢየሱስ ወደ ጀልባው በገቡ ጊዜ፣ ነፋሱ መንፈሱን ወዲያውኑ አቆመና ጸጥ አለ። ደቀ መዛሙርቱ ተደነቁ። “በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ” በማለት ለኢየሱስ ሰገዱለት።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 14፡22-23፤ ማርቆስ 6፡45-52፤ ዮሐንስ 6፡16-21።