am_obs/content/28.md

3.6 KiB

28. ባለ ጠጋው ወጣት

OBS Image

አንድ ቀንአንድ ባለጠጋወጣት ወደ ኢየሱስ መጣና፣ “ቸር መምህር፣ የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ?” ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስ፣ “ስለ ምን ‘ቸር’ ትለኛለህ? ቸርአንድ ብቻአለ፣ እርሱም እግዚአብሔር ነው።ነገር ግንአንተ የዘላለም ሕይወት እንዲኖርህ ከፈለግህ ለእግዚአብሔር ሕግታዘዝ” አለው።

OBS Image

“የትኞቹን ልታዘዝ?” ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፣ “አትግደል። አታመንዝር። አትስረቅ። አትዋሽ። አባትህንና እናትህን አክብር፣ ባልጀራህንምእንደ ራስህ ውደድ።”

OBS Image

ነገር ግን ወጣቱ፣ “ከልጅነቴጀምሮ እነዚህንሕጎች ሁሉ ፈጽሜአለሁ። ለዘላለም ለመኖርሌላስ ምን ማድረግ ያስፈልገኛል?” አለ። ኢየሱስ ዐየውና ወደደው።

OBS Image

ኢየሱስ፣ “ፍጹም ለመሆን ብትፈልግ፣ ያለህን ንብረት ሁሉሽጥና ገንዘቡን ለድሆች ስጥ፣ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ። ከዚያም በኋላ ናና ተከተለኝ” ብሎመለሰለት።

OBS Image

ወጣቱ፣ ኢየሱስ የተናገረውን በሰማ ጊዜ፣ በጣም ባለ ጠጋ ነበርና ያለውን ነገር ሁሉ መስጠት ስላልፈለገ በጣም ዐዘነ። ከኢየሱስ ፊቱን አዞረና ሄደ።

OBS Image

በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፣ “ለባለ ጠጎች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እጅግ አስቸጋሪ ነው! አዎ፣ ባለ ጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል።”

OBS Image

ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ የተናገረውን በሰሙ ጊዜ ደነገጡና፣ “ታዲያ ማን ሊድን ይችላል?” አሉ።

OBS Image

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ተመለከተና፣ “ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል” አለ።

OBS Image

ጴጥሮስ ኢየሱስን፣ “እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ። ዋጋችን ምን ይሆን?” አለው።

OBS Image

ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፣ “ስለ እኔ ቤቶችን፣ ወንድሞችን፣ እኅቶችን፣ አባትን፣ እናትን ወይም ንብረትን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል። ነገር ግን ፊተኞች የሆኑ ብዙዎች ኋለኞች፣ ኋለኞችም የሆኑ ብዙዎች ፊተኞች ይሆናሉ።”

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 19፡16-30፤ ማርቆስ 10፡17-31፤ ሉቃስ 18፡18-30።