am_obs/content/26.md

4.3 KiB

26. ኢየሱስ አገልግሎቱን ጀመረ

OBS Image

ኢየሱስ የሰይጣንን ፈተና ካሸፈነ በኋላ፣ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይኖርበት ወደ ነበረው ወደገሊላ አውራጃ ተመለሰ። ኢየሱስ ከቦታ ወደ ቦታ እየሄደ አስተማረ።ሁሉም ሰው ስለ እርሱ መልካም ይናገሩ ነበር።

OBS Image

ኢየሱስ በልጅነቱ ወደ ኖረበት ወደ ናዝሬትከተማ ተመለሰ። በሰንበት ወደ አምልኮ ቦታ ሄደ።ያነብ ዘንድ የነቢዩን የኢሳይያስን ጥቅልልጽሑፍ ሰጡት። ኢየሱስ ጥቅልል ጽሑፉን ከፍቶ በከፊል ለሕዝቡ አነበበላቸው።

OBS Image

ኢየሱስ፣ “ለድሆች የምሥራችን፣ ለተማረኩት ነጻትን፣ ለዕውሮች ማየትን፣ ለታሰሩትም መፈታትን እሰብክዘንድ እግዚአብሔር መንፈሱን ሰጥቶኛል።ይህች የተወደደችውየጌታ ዓመት ነች” ብሎ አነበበ።

OBS Image

ከዚያም ኢየሱስ ተቀመጠ። ሁላቸውም በቅርበት ተመለከቱት። ልክ አሁን ያነበበው የእግዚአብሔር ቃል ምንባብ መሲሑን ያመለክት ነበር። ኢየሱስ፣“ይህ ያነበብኩላችሁ ቃል ልክአሁን እየተፈጸመ ነው” አለ።ሕዝቡ ሁሉ ተደነቁ። “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን?” አሉ።

OBS Image

ከዚያም ኢየሱስ፣“ነቢይ በገዛ አገሩ እንደማይከበር እውነትነው፣ በነቢዩ ኤልያስ ዘመን፣ በእስራኤል ብዙ መበለቶች ነበሩ።ነገር ግን ለሦስትዓመት ተኩል ዝናብ ባልዘነበ ጊዜ እግዚአብሔር ኤልያስን በተለየአገር እንጂ በእስራኤልያለች መበለትን እንዲረዳ አልላከውም።”

OBS Image

ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መናገሩን ቀጠለ፣ “በነቢዩ ኤልሳዕ ዘመንም በእስራኤል የቆዳ ሕመም የያዛቸው ብዙ ሰዎች ነበሩ። ነገር ግን ኤልሳዕ አንዳቸውንም አልፈወሰም። የእስራኤል ጠላቶች አዛዥ የነበረውን የንዕማንን ቆዳ በሽታ ብቻ ፈወሰ።” ኢየሱስን ይሰሙ የነበሩት ሕዝብ አይሁዳውያን ነበሩ። ስለዚህ ይህን ሲናገር በሰሙት ጊዜ ተናደዱበት።

OBS Image

የናዝሬት ሕዝብ ኢየሱስን ከአምልኮው ቦታ ጐተቱትና ወርውረው ሊገድሉት ወደ ተራራውአፋፍ ወሰዱት።ነገር ግን ኢየሱስ በሕዝቡ መካከል ተራመደና ወደ ናዝሬትከተማ ሄደ።

OBS Image

ከዚያም ኢየሱስ በገሊላ አውራጃ ሁሉ ተዘዋወረ፣ ብዙ ሕዝብም ወደ እርሱ መጡ። ማየት፣ መራመድ፣ መስማት፣ ወይም መናገር የማይችሉትን ጨምሮ ብዙ የታመሙ ወይም የአካል ጕዳተኞች የሆኑ ሰዎችን አመጡ።

OBS Image

አጋንንት የነበሩባቸው ብዙ ሰዎችን ወደ ኢየሱስ አመጡ። በኢየሱስ ትእዛዝ አጋንንቱ ከሰዎቹ ወጡ፣ ብዙ ጊዜም፣ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ!” ብለው ጮኹ። ሕዝቡ ተደነቁና እግዚአብሔርን አመለኩ።

OBS Image

ከዚያም ኢየሱስደቀ መዛሙርቱ ተብለው የተጠሩትን ዐሥራ ሁለት ሰዎች መረጠ። ሐዋርያቱ ከኢየሱስ ጋር ተጓዙና ከእርሱ ተማሩ።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 4፡12-25፤ ማርቆስ 1፡14-15፣ 35-39፤ 3፡13-21፤ ሉቃስ 4፡14-30፣ 38-44።