am_obs/content/25.md

2.7 KiB

25. ሰይጣን ኢየሱስን ፈተነው

OBS Image

ኢየሱስ ከተጠመቀበኋላ ወዲያውኑ፣ መንፈስቅዱስ ወደምድረ በዳ ወሰደው፣ እዚያምአርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾመ። ከዚያም ሰይጣን ወደ ኢየሱስመጣና ኃጢአት እንዲሠራ ኢየሱስን ፈተነው።

OBS Image

“የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንክ፣ መብላት ትችል ዘንድ እነዚህን ድንጋዮች ወደእንጀራ ለውጥ” በማለት ሰይጣን ኢየሱስን ፈተነው።

OBS Image

ኢየሱስ፣ “‘ሰዎች ለመኖር እንጀራ ብቻ አያስፈልጋቸውም፣ነገር ግን እግዚአብሔር የሚናገረው እያንዳንዱ ቃል ያስፈልጋቸዋል’ተብሎ በእግዚአብሔር ቃል ተጽፎአል!” ብሎ መለሰለት።

OBS Image

ከዚያም ሰይጣን ኢየሱስን ወደ ቤተ መቅደስ ጫፍ ወሰደውና፣ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ ራስህን ወደ ታች ወርውር፣ ምክንያቱም፣ ‘ድንጋይ እግርህን እንዳይመታህ ይሸከሙህዘንድ እግዚአብሔር መላእክቱንያዛል ተብሎ ተጽፎል’” አለ።

OBS Image

ነገር ግን ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ቃል በመጥቀስ ለሰይጣን መለሰለት። “በእግዚአብሔር ቃል፣ ‘ጌታ አምላክህን አትፈታተነው’ በማለት ሕዝቡን ያዛል አለ።’”

OBS Image

ከዚያም ሰይጣን የዓለምን መንግሥታትና ክብራቸውን ሁሉ ዐሳየውና፣ “ወድቀህ ብትሰግድልኝይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ” አለ።

OBS Image

ኢየሱስ፣ “ሂድ፣ አንተ ሰይጣን! በእግዚአብሔር ቃልሕዝቡን፣ ‘ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻአምልክ’ ብሎአዞአል” አለው።

OBS Image

ኢየሱስ ለሰይጣንፈተና አልተሸነፈም፣ ስለዚህ ሰይጣን ተወው። ከዚያ በኋላ መላእክት መጥተው ኢየሱስን አገለገሉት።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 4፡1-11፤ ማርቆስ 1፡12-13፤ ሉቃስ 4፡1-13።