am_obs/content/24.md

3.9 KiB

24. ዮሐንስ ኢየሱስን አጠመቀ

OBS Image

የዘካርያስና የኤልሳቤጥ ልጅ ዮሐንስ አደገና ነቢይ ሆነ። በምድረ በዳ ኖረ፣ የበረሐ ማርና አንበጣ ተመገበ፣ ከግመል ፀጉር የተሠራ ልብስም ለበሰ።

OBS Image

ብዙ ሕዝብ ዮሐንስን ለመስማት ወደ ምድረ በዳ መጡ። እርሱም፣ “የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” በማለት ሰበከላቸው።

OBS Image

ሕዝቡ የዮሐንስን መልእክት በሰሙ ጊዜ፣ አብዛኞቻቸው ኃጢአታቸውን ተናዘዙ፣ ዮሐንስም አጠመቃቸው። ብዙ የሃይማኖት መሪዎች ደግሞ በዮሐንስ ሊጠመቁ መጡ፣ ነገር ግን ንስሐ አልገቡም ወይም ኃጢአታቸውን አልተናዘዙም።

OBS Image

ዮሐንስ ለሃይማኖት መሪዎቹ እንዲህ አላቸው፣ “እናንተ መርዛማ እባቦች! ንስሐ ግቡና ድርጊታችሁን ለውጡ። መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቈረጥና ወደ እሳት ይጣላል።” ዮሐንስ ነቢያት “እነሆ፣ መንገድህን የሚያዘጋጅ መልእክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ።” በማለት የተናገሩትን ፈጽመ።

OBS Image

አንዳንድ አይሁዶች መሲሕ ስለ መሆኑ ዮሐንስን ጠየቁት። ዮሐንስ እንዲህ ብሎ መለሰ፣ “እኔ መሲሑ አይደለሁም፣ ነገር ግን ከእኔ በኋላ የሚመጣ አንድ ሰው አለ። የጫማውን ማሰሪያ ልፈታ እንኳ የማይገባኝ በጣም ታላቅ ነው።”

OBS Image

በቀጣዩ ቀን፣ ኢየሱስ በዮሐንስ ለመጠመቅ መጣ። ዮሐንስ ባየው ጊዜ፣ “ተመልከቱ! እነሆ፣ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” አለ።

OBS Image

ዮሐንስ ኢየሱስን፣ “እኔ አንተን ለማጥመቅ ተገቢ ሰው አይደለሁም። በዚህ ፈንታ አንተ እኔን ማጥመቅ አለብህ እንጂ” አለው። ኢየሱስ ግን፣ “መደረግ ያለበት ትክክለኛ ነገር ነውና አንተ እኔን ማጥመቅ ይገባሃል” አለ። ስለዚህ ኢየሱስ ከቶ ኃጢአት ባይሠራም እንኳ ዮሐንስ ኢየሱስን አጠመቀው።

OBS Image

ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ ከውኃው እንደ ወጣ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ በርግብ አምሳል ታየና ወርዶ በእርሱ ላይ ዐረፈ። በዚሁ ጊዜ የእግዚአብሔር ድምፅ ከሰማይ፣ “አንተ እኔ የምወድህ ልጄ ነህ፣ በአንተም በጣም ደስ ብሎኛል” ብሎ ተናገረ።

OBS Image

እግዚአብሔር ለዮሐንስ፣ “መንፈስ ቅዱስ ይወርድና አንተ በምታጠምቀው ሰው ላይ ያርፋል። ሰውዬው የእግዚአብሔር ልጅ ነው” ብሎ ተናግሮት ነበር። አንድ አምላክ ብቻ አለ። ነገር ግን ዮሐንስ ኢየሱስን ባጠመቀው ጊዜ፣ እግዚአብሔር አብ ሲናገር ሰማ፣ እግዚአብሔር ወልድን ዐየ፣ እርሱም ኢየሱስ ነው፣ እንዲሁም መንፈስ ቅዱስን ዐየ።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 3፤ ማርቆስ 1፡9-11፤ ሉቃስ 3፡1-23።