am_obs/content/22.md

4.0 KiB

22. የዮሐንስ መወለድ

OBS Image

አስቀድሞ እግዚአብሔር በመላእክቱና በነቢያቱ በኩል ለሕዝቡ ተናግሮ ነበር። ነገር ግን ለእነርሱ ያልተናገረባቸው 400 ዓመታት አለፉ። በድንገት አንድ መልአክ ዘካርያስ ተብሎ ወደሚጠራ ሽማግሌ ካህን ከእግዚአብሔር ዘንድ መልእክት ይዞ መጣ። ዘካርያስና ሚስቱ ኤልሳቤጥ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ነበሩ፣ ነገር ግን እርስዋ ልጆችን መውለድ አልቻለችም ነበር።

OBS Image

መልአኩ ዘካርያስን አለው፣ “ሚስትህ ወንድ ልጅ ትወልዳለች። ዮሐንስ ብለህ ተጠራዋለህ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ ይሞላል፣ ሕዝቡንም ለመሲሑ ያዘጋጃል!” ዘካርያስ፣ “ሚስቴና እኔ ልጆችን ለመውለድ በጣም አርጅተናል! ይህ እንደሚሆን እንዴት ዐውቃለሁ?” ብሎ መለሰ።

OBS Image

መልአኩ ለዘካርያስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፣ ይህን የምሥራች እንዳመጣላችሁ እግዚአብሔር ላከኝ። ስላላመንከኝ፣ ልጁ እስኪወለድ ድረስ መናገር አትችልም።" ወዲያኑ ዘካርያስ መናገር አልቻለም። ከዚያ በኋላ መልአኩ ከዘካርያስ ተለየ። ዘካርያስም ወደ ቤት ተመለሰ ሚስቱም ፀነሰች።

OBS Image

ኤልሳቤጥ የስድስት ወር ነፍሰ ጡር በነበረች ጊዜ፣ ያው መልአክ በድንገት ስምዋ ማርያም ለተባለ ለኤልሳቤጥ ዘመድ ተገለጠ። እርስዋ ድንግል ነበረችና ልታገባ ዮሴፍ ለተባለ ሰው ታጭታ ነበር። መልአኩ፣ “ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ። ስሙን ኢየሱስ ትዪዋለሽ። እርሱም የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ይባላል ለዘላለምም ገዥ ይሆናል” አለ።

OBS Image

ማርያም “እኔ ድንግል ስለ ሆንኩ፣ ይህ እንዴት ይሆናል?” ብላ መለሰች። መልአኩ እንዲህ ብሎ አብራራ፣ “መንፈስ ቅዱስ ወደ አንቺ ይመጣል፣ የልዑል ኃይል ይጸልልሻል። ስለዚህ ልጁ ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይሆናል።” ማርያም አመነች መልአኩ ያለውንም ተቀበለች።

OBS Image

መልአኩ ለማርያም ከተናገረ በኋላ ወዲያወኑ፣ ሄደችና ኤልሳቤጥን ጐበኘቻት። ኤልሳቤጥ የማርያምን ሰላምታ እንደ ሰማች፣ የኤልሳቤጥ ልጅ በሆዷ ውስጥ ዘለለ። ሴቶቹ እግዚአብሔር ስላደረገላቸው ነገር አብረው ሐሤት አደረጉ። ማርያም ኤልሳቤጥን ለሦስት ወራት ከጐበኘቻት በኋላ፣ ማርያም ወደ ቤትዋ ተመለሰች።

OBS Image

ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅዋን ከወለደች በኋላ፣ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ መልአኩ እንዳዘዘው ሕፃኑን ዮሐንስ ብለው ሰየሙት። በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ለዘካርያስ እንደ ገና እንዲናገር ፈቀደለት። ዘካርያስ እንዲህ አለ፣ “ሕዝቡን ዐስቦአልና እግዚአብሔር ይመስገን! አንተም ልጄ፣ ለኃጢአታቸው ይቅርታ መቀበል እንዴት እንደሚችሉ ለሕዝቡ የምትናገር የልዑል እግዚአብሔር ነቢይ ትባላለህ!”

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከሉቃስ 1።