am_obs/content/18.md

5.5 KiB

18. የተከፈለው መንግሥት

OBS Image

ከብዙ ዓመታት በኋላ፣ዳዊት ሞተ፣ ልጁ ሰሎሞንም በእስራኤል ላይይገዛ ጀመር። እግዚአብሔር ለሰሎሞን ተናገረውና በይበልጥ ምን እንደሚፈልግ ጠየቀው። ሰሎሞን ጥበብን በለመነጊዜ፣ በዓለም ላይእጅግ በጣም ጠቢብ ሰው አደረገው። ሰሎሞን ብዙ ነገሮችን ተማረናበጣም ጠቢብ ፈራጅ ሆነ። ደግሞም እግዚአብሔርበጣም ባለ ጠጋ አደረገው።

OBS Image

ሰሎሞን በኢየሩሳሌም አባቱ ዳዊት ያቀደውንና ለግንባታው የሚያስፈልጉ ነገሮች የሰበሰበለትን ቤተ መቅደሱን ሠራ። አሁን ሕዝቡ በመገናኛው ድንኳ ፈንታ በቤተ መቅደሱ እግዚአብሔርን አመለኩ መሥዋዕትንም አቀረቡለት። እግዚአብሔር መጥቶ በቤተ መቅደሱ ተገኘ፣ በዚያም ከሕዝቡ ጋር ኖረ።

OBS Image

ነገር ግን ሰሎሞን ከሌሎች አገሮች የሆኑ ሴቶችን ወደደ። ከሞላ ጐደል 1000 የሚሆኑ ብዙ ሴቶችን በማግባት ለእግዚአብሔር አልታዘዘም! ከእነዚህ ሴቶች ብዙዎቹ ከውጪ አገሮች መጡ፣ ጣዖቶቻቸውን አመጡና እነርሱኑ ማምለካቸውን ቀጠሉ። ሰሎሞን በሸመገለ ጊዜ፣ እርሱም ደግሞ የእነርሱን አማልክት አመለከ።

OBS Image

እግዚአብሔር በሰሎሞን ላይ ተቈጣ፣ ሰሎሞን ባለመታመኑ እንደ መቀጣጫ ሰሎሞን ከሞተ በኋላ የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ሁለት መንግሥታት እንደሚከፍል ተናገረ።

OBS Image

ሰሎሞን ከሞተ በኋላ ልጁ ሮብዓም ነገሠ። ሮብዓም ሞኝ ነበረ። የእስራኤል ሕዝብ በሙሉ ንጉሥነቱን ሊያጸድቁለት ተሰብስበው መጡ። ሰሎሞን ብዙ ከባድ ሥራ እንዳሠራቸውና ብዙ ግብር እንዳስከፈላቸው ለሮብዓም ቅሬታቸውን ተናገሩ።

OBS Image

ሮብዓም በሞኝነት እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፣ “አባቴ ሰሎሞን ከባድ ሥራ አሠርቶናል ብላችሁ ዐስባችኋል፣ ነገር ግን እኔ ከእርሱ የባሰ ከባድ ሥራ አሠራችኋለሁ፣ ከእርሱ የባሰም በኃይል እቀጣችኋለሁ።”

OBS Image

ዐሥሩ የእስራኤል ሕዝብ ነገዶች በሮብዓም ላይ ዓመፁ። ሁለት ነገዶች ብቻ ለእርሱ ባላቸው ታማኝነት ቀጠሉ። እነዚህ ሁለት ነገዶች የይሁዳ መንግሥት ሆኑ።

OBS Image

በሮብዓም ላይ ያመፁት ሌሎቹ ዐሥር የእስራኤል ሕዝብ ነገዶች ኢዮርብዓም የተባለውን ሰው ንጉሣቸው አድርገው ሾሙት። በምድሪቱ ሰሜናዊ ክፍል መንግሥታቸውን አቋቋሙ የእስራኤል መንግሥት ተብለውም ተጠሩ።

OBS Image

ኢዮርብዓም በእግዚአብሔር ላይ ዓመፀና ሕዝቡ ኃጢአት እንዲሠሩ አደረገ። በይሁዳ መንግሥት ባለው ቤተ መቅደስ እግዚአብሔርን በማምለክ ፈንታ ሕዝቡ ያመልኩአቸው ዘንድ ሁለት ጣዖታትን ሠራላቸው።

OBS Image

የይሁዳና የእስራኤል መንግሥታት ጠላቶች ሆኑና ብዙ ጊዜ እርስ በርስ ተዋጉ።

OBS Image

በዐዲሲቱ የእስራኤል መንግሥት፣ ነገሥታቱ ሁሉ ክፉዎች ነበሩ። ከእነዚህ ነገሥታት አብዛኞቹ፣ በእነርሱ ቦታ መንገሥ በፈለጉ ሌሎች እስራኤላውያን ተገደሉ።

OBS Image

ነገሥታቱ ሁሉና አብዛኞቹ የእስራኤል መንግሥት ሕዝብ ጣዖትን አመለኩ። የጣዖት አምልኮአቸው ብዙውን ጊዜ ግብረ ገብነት የጐደለው የግብረ ሥጋ ግንኙነትና አንዳንድ ጊዜ ልጆችን መሠዋትን ያካተተ ነበር።

OBS Image

የይሁዳ ነገሥታት የዳዊት ዝርያዎች ነበሩ። ከእነዚህ ነገሥታት አንዳንዶቹ በትክክል የገዙና እግዚአብሔርን ያመለኩ ጥሩ ሰዎች ነበሩ። ነገር ግን አብዛኞቹ ነገሥታት ክፉዎችና ብልሹዎች ነበሩ፣ ጣዖታትንም ያመልኩ ነበር። አንዳንዶቹ ነገሥታት ልጆቻቸውን እንኳ ለሐሰት አማልክት ሠውተዋል። ደግሞም አብዛኞቹ የይሁዳ ሕዝብ በእግዚአብሔር ላይ ዓመፁ ሌሎች አማልክትንም አመለኩ።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከ1ኛ ነገሥት 1-6፤ 11-12።