am_obs/content/10.md

4.6 KiB

10. ዐሥሩ መቅሠፍቶች

OBS Image

ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ሄዱ። “የእስራኤል አምላክ ‘ሕዝቤንልቀቅ !’” ይላሃል አሉት። ፈርዖን አልሰማቸውም። እስራኤላውያን ነጻ ሆነው እንዲሄዱ በማድረግፈንታ ከዚህም የከበደ ሥራ እንዲሠሩ አስገደዳቸው!

OBS Image

ፈርዖን ሕዝቡን አልለቅም ማለቱን ቀጠለ፣ ስለዚህ እግዚአብሔር በግብፅ ላይ ዐሥር መቅሠፍቶችን ላከ። እግዚአብሔር በእነዚህ መቅሠፍቶች በኩል ከፈርዖንና ከግብፅ አማልክት ሁሉ ይልቅ ኃያል መሆኑን ለፈርዖን ዐሳየው።

OBS Image

እግዚአብሔር የዓባይን ውሃ ወደ ደም ለወጠው፣ ነገር ግን ፈርዖን አሁንም እስራኤላውያንን አልለቀቃቸውም።

OBS Image

እግዚአብሔር በግብፅ ሁሉ ላይ እንቁራሪቶችን ላከ። ፈርዖን ሙሴን እንቁራሪቶቹን እንዲያርቅ ለመነው። ሆነም ቀረ ግን እንቁራሪቶቹ ሁሉ ሞቱ። ፈርዖን ልቡን አደነደነና እስራኤላውያንን ከግብፅ እንዲወጡ አልለቀቃቸውም።

OBS Image

ስለዚህ እግዚአብሔር ትንኞችን ላከ። ከዚያም ዝንቦችን ላከ። ፈርዖን ሙሴንና አሮንን ጠራና መቅሠፍቱን ካቆሙ እስራኤላውያን ከግብፅ መሄድ እንደሚችሉ ነገራቸው። ሙሴ በጸለየ ጊዜ እግዚአብሔር ዝንቦችን ሁሉ ከግብፅ አስወገደ። ነገር ግን ፈርዖን ልቡን አደነደነና ሕዝቡን አልለቀቀም።

OBS Image

ቀጥሎ እግዚአብሔር የግብፃውያን ከብቶች ሁሉ ታመው እንዲሞቱ አደረገ። ነገር ግን የፈርዖን ልብ ደነደነና እስራኤላውያንን አልለቀቀም።

OBS Image

ከዚያም እግዚአብሔር በፈርዖን ፊት ዐመድ ወደ ሰማይ እንዲበትን ለሙሴ ነገረው። ዐመዱን በበተነ ጊዜ በግብፃውያን ላይ የሚያም ቊስል ሆነ፣ በእስራኤላውያን ላይ ግን ቊስሉ አልሆነባቸውም። እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ አደነደነ፣ ፈርዖንም እስራኤላውያንን አልለቀቀም።

OBS Image

ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር በግብፅ ያለውን አብዛኛውን ቡቃያ ያጠፋና ከቤት ውጪ የነበረውን ማንኛውንም ሰው የገደለ በረዶ ላከ። ፈርዖን ሙሴንና አሮንን ጠርቶ፣ “በድዬአለሁ። መሄድ ትችላላችሁ” ብሎ ነገራቸው። ስለዚህ ሙሴ ጸለየ፣ በረዶውም ከሰማይ መዝነቡን አቆመ።

OBS Image

ነገር ግን ፈርዖን እንደ ገና ኃጢአት ሠራ ልቡንም አደነደነ። እስራኤላውያንን አልለቀቀም።

OBS Image

ስለዚህ እግዚአብሔር በግብፅ ላይ የአንበጣዎችን መንጋ አመጣ። እነዚህ አንበጣዎች በረዶው ያላጠፋውን ሰብል ሁሉ በሉት።

OBS Image

ከዚያም እግዚአብሔር ለሦስት ቀን የቆየ ጨለማ ላከ። ግብፃውያን ከቤቶቻቸው እስከማይወጡ ድረስ በጣም ጨልሞ ነበር። እስራኤላውያን በሚኖሩበት ስፍራ ግን ብርሃን ነበረ።

OBS Image

ከእነዚህ ዘጠኝ መቅሠፍቶች በኋላ እንኳ ፈርዖን አሁንም እስራኤላውያንን አልለቅም አለ። ፈርዖን ስለማይሰማ፣ እግዚአብሔር አንድ የመጨረሻ መቅሠፍት ለመላከ ወሰነ። ይህ የፈርዖንን ዐሳብ ይለውጣል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘጸአት 5-10።