am_obs/content/09.md

5.8 KiB

9. እግዚአብሔር ሙሴን ጠራው

OBS Image

ዮሴፍ ከሞተ በኋላ ዘመዶቹ በሙሉ በግብፅ ቆዩ። እነርሱና ዘሮቻቸው ለብዙ ዓመታት እዚያ መኖራቸውን ቀጠሉ፤ ብዙ ልጆችንም አፈሩ፤ እነርሱ እስራኤላውያን ተብለው ተጠሩ።

OBS Image

ከመቶዎች ዓመታት በኋላ የእስራኤላውያን ቊጥር እየበዛ መጣ። ግብፃውያንም ዮሴፍንና እነርሱን ለመርዳት ያደረገውን ሁሉ ዘነጉ። እስራኤላውያን እየበዙ በመምጣታቸው ግብፃውያን ፈሯቸው። ስለዚህ በዚያን ጊዜ ግብፅን ያስተዳድር የነበረው ፈርዖን እስራኤሎችን ለግብፃውያን ባሪያዎች አደረጓቸው።

OBS Image

ግብፃውያን እስራኤላውያንን የግንብ ሥራ እንዲሠሩ፣ ከተማውን ሁሉ እንዲገነቡ በማድረግ በኃይል ያስገድዷቸው ነበር። ከባድ ሥራ ሕይወታቸውን አስቸጋሪ አደረገው። እግዚአብሔር ግን ባረካቸው ብዙ ልጆችም ነበሯቸው።

OBS Image

ፈርዖን እስራኤላውያን ብዙ ሕፃናት እንዳሏቸው አየ፤ ስለዚህ ፈርዖን ከእስራኤላውያን ወንዶች ልጆች ሲወለዱ አባይ ወንዝ ውስጥ በመወርወር እንዲገድሉ ሕዝቡን አዘዘ።

OBS Image

አንዲት እስራኤላዊት ሴት ወንድ ልጅ ወለደች፤ እርሷና ባለቤቷ የቻሉትን ያህል ልጁን ደበቁ።

OBS Image

የልጁ ወላጆች ልጁን ሊደብቁት ባልቻሉ ጊዜ ልጁን በሚንሳፈፍ ቅርጫት ውስጥ አድርገው በአባይ ወንዝ ዳር ባለው ቄጤማ ፊት ለፊት እንዳይገደል ሊያድኑት ወንዙ ላይ ለቀቁት። ታላቅ እህቱም የሚሆንበትን ለማየት በቅርብ ትከታተለው ነበር።

OBS Image

የፈርዖን ሴት ልጅ ቅርጫት አየችና በውስጡ ያለውን ተመለከተች። ሕፃኑን ባየች ጊዜ እንደ ልጇ አድርጋ ወሰደችው። እርሷም ልጁን የምትንከባከብ እስራኤላዊት ሴት ቀጠረች። የቀጠረቻትም ሴትዮ የገዛ ልጁ እናት መሆኗን ሳታውቅ ነበር። ልጁም ሲያድግና የናቱን ጡት መጥባት ባቆመ ጊዜ ሴትዮዋ ወደ ፈርዖን ልጅ መለሰችው ስሙንም “ሙሴ” ብለው ጠሩት።

OBS Image

አንድ ቀን ሙሴ ባደገ ጊዜ አንድ ግብፃዊ እስራኤላዊ የሆነን ባሪያ ሲመታው አየ ሙሴም እስራኤላዊ ወገኑን ሊያድነው ሞከረ።

OBS Image

ሙሴ ማንም የማያይ መስሎት ግብፃዊውን ገድሎ ቀበረው። ነገር ግን ሙሴ ያደረገውን አንድ ሰው አይቶታል።

OBS Image

ሙሴ ያደረገውን ፈርዖን በሰማ ጊዜ ሊገድለው ሞከረ። ሙሴ ግን ከፈርዖን ወታደሮች ነፍሱን ወደሚያድንበት ከግብፅ ወደ ምድረ በዳ ሸሸ።

OBS Image

ከግብፅ ሩቅ በሆነ ምድረ በዳ ሙሴ የበጐች እረኛ ሆነ። ከዚያም አገር ሚስት አግብቶ ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደ።

OBS Image

አንድ ቀን ሙሴ በጐቹን እየጠበቀ ሳለ እሳት የሚነድበት ቊጥቋጦ ተመለከተ ይሁን እንጂ ቊጥቋጦው አልተቃጠለም፤ ሙሴም በደንብ ለማየት ወደ ቊጥቋጦው ጠጋ አለ። ወደሚቃጠለው ቊጥቋጦ ጠጋ ሲል የእግዚአብሔር ድምፅ “ሙሴ በቅዱስ ስፍራ ቆመሃልና ከእግርህ ጫማህን አውልቅ” አለው።

OBS Image

እግዚአብሔርም አለ “የሕዝቤን መከራ አይቻለሁና ወደ ፈርዖን እልክሃለሁ እስራኤልንም ከግብፅ ባርነት ነጻ ታወጣቸዋለህ። ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ተስፋ የሰጠኋቸውን የከነዓንን ምድር እሰጣቸዋለሁ።”

OBS Image

ሕዝቡ ማንላከህ ብለው ቢጠይቁኝ ምን እላቸዋለሁ ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርምሙሴን “እኔ ያለሁና የምኖር ነኝ ስለዚህ‘ያለና የሚኖር’ ልኮኛልብለህ ንገራቸው” አለው።

OBS Image

ሙሴ ስለ ፈራ ወደ ፈርዖን መሄድ አልፈለገም። ምክንያቱም የንግግር ችሎታ የለኝም ብሎ በማሰቡ ነበር። ስለዚህም እግዚአብሔር የሙሴን ወንድም አሮንን አብሮት እንዲሄድና ሙሴን እንዲረዳው ላከው። እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን ፈርዖን ሕዝቡን አለቅም በሚል ልቡን ሊያደነድን እንደሚችል አስጠነቀቃቸው።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘፅአት 1-4።