am_obs/content/07.md

4.1 KiB

7. እግዚአብሔር ያዕቆብን ባረከ

OBS Image

ልጆቹም እንዳደጉ ያዕቆብ ከእናቱ ጋር በቤት መቆየትን ይወድ ነበር። ኤሳው ግን አደን ማደን ይወድ ነበር። ርብቃ ያዕቆብን ትወድደው ነበር፣ ይስሐቅ ግን ኤሳውን ይወድደው ነበር።

OBS Image

ከዕለታት አንድ ቀን ኤሳው ከአደን ተመልሶ ሲመጣ በጣም ተርቦ ነበር። ኤሳው ያዕቆብን “እባክህ ካዘጋጀኸው ምግብ ትንሽ ስጠኝ” አለው። ያዕቆብም በመጀመሪያ የብኩርናህን መብት ስጠኝ ሲል መለሰለት። ስለዚህም ኤሳው የብኩርናውን መብት ለያዕቆብ ሰጠው ከዚያም ያዕቆብ ከሠራው ምግብ ሰጠው።

OBS Image

ይስሐቅ በረከቱን ለኤሳው ሊሰጠው ፈለገ።ነገር ግንይህን ከማድረጉበፊት ርብቃና ያዕቆብ ይስሐቅን አታለሉት። ያዕቆብ ኤሳውንመስሎ ወደ ይስሐቅ ቀረበ። ይስሐቅ አርጅቶነበር ማየትም አይችልም ነበር። ስለዚህም ያዕቆብ የኤሳውን ልብሶችለብሶ የፍየልለምድ በአንገቱናበእጁ አድርጎ ወደ ይስሐቅ በመቅረብ ይስሐቅን አታለለው።

OBS Image

ያዕቆብ ወደ ኤሳው መጣና እንዲህ አለው፣ “እኔ ኤሳው ነኝ መጥቻለሁና ልትባርከኝ ትችላለህ” ይስሐቅ የፍየሉን ፀጉር ዳሰሰና የልብሱንም ጠረን አሽትቶ ኤሳው እንደ ሆነ አሰበና ባረከው።

OBS Image

ያዕቆብ የብኵርና መብቱንና በረከቱን አታልሎ ስለ ወሰደበት ኤሳው ያዕቆብን ጠላው አባታቸው ከሞተ በኋላ ሊገድለውም አሰበ።

OBS Image

ነገር ግን ርብቃ የኤሳውን እቅድ ሰማች። ስለዚህም እሷና ይስሐቅ ከዘመዶቹ ጋር እንዲኖር ወደ ሩቅ አገር ያዕቆብን ሰደዱት።

OBS Image

ያዕቆብ ለረዥም ዓመታት ከርብቃ ዘመዶች ጋር ኖረ። በዚያም ጊዜ ትዳር መስርቶ 12 ወንዶች ልጆችና 1 ሴት ልጅ ወለደ። እግዚአብሔርም በጣም አበለጸገው።

OBS Image

በከነዓን ከኖረበት ከሃያ (20) ዓመታት በኋላ ያዕቆብ ከቤተ ሰቡ፣ ከሠራተኞቹና ከመንጋው ሁሉ ጋር ወደ ከነዓን ምድር ለመመለስ ወሰነ።

OBS Image

ኤሳው አሁንም ሊገድለኝ ያስብ ይሆናል ብሎ በልቡ ስላሰበ ያዕቆብ ፈራ። ስለዚህም የእጅ መንሻ እንዲሆነው የብዙ ከብቶች መንጋ ስጦታ አድርጎ ለኤሳው ላከለት። ከብቶቹን ያመጡለት የያዕቆብ አገልጋዮች ኤሳውን “አገልጋይህ ያዕቆብ እነዚህን ከብቶች ልኮልሃል እርሱም በቅርቡ ይመጣል” አሉት።

OBS Image

ኤሳው ግን ቀድሞውኑ ያዕቆብን ይቅር ብሎት ስለ ነበር ዳግም ለመገናኘት ደስተኞች ነበሩ። ያዕቆብ በከነዓን ምድር በሰላም ኖረ፤ ከዚያም ይስሐቅ ሞተ ያዕቆብና ኤሳው ቀበሩት እግዚአብሔር ለአብርሃም የገባለት የቃል ኪዳኑ ተስፋ አሁን ከይስሐቅ ወደ ያዕቆብ ተላለፈ።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘፍጥረት 25፡27-33፡20።