am_obs/content/04.md

4.2 KiB

4. የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ከአብርሃም ጋር

OBS Image

ከጥፋት ውሃው ከብዙ ዓመታትበኋላ ሕዝቦች በዓለም ላይ እንደገና በዙ።ሁሉም አንድ አይነትቋንቋ ይናገሩ ነበር። እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው ምድርን ከመሙላትይልቅ በአንድነት ተሰብስበውከተማ ሠሩ።

OBS Image

እነርሱም በጣም ትምክህተኞችና እግዚአብሔር ለተናገራቸው ነገር ያልተጠነቀቁ ነበሩ። እንዲያውም ወደ ሰማይ ሊደርሱ ረጅም ሕንጻ መገንባት ጀመሩ። እግዚአብሔርም እነዚህ ሰዎች ክፉ መሥራታቸውንና በዚህም መቀጠላቸውን አየ። ከዚህም የከፋ ኃጢአት ማድረግ ይችሉም ነበር።

OBS Image

ስለዚህም እግዚአብሔር ቋንቋቸውን ወደ ብዙ የተለያዩ ቋንቋዎች ለወጠና ሕዝቡን በዓለም ሁሉ በተናቸው። ሊሠሩት የጀመሩት ከተማ ስም ባቢሎን ይባላል። የስሙም ትርጓሜ የተደባለቀ ወይም ግራ የተጋባ ማለት ነው።

OBS Image

ከመቶ ዓመታት በኋላ እግዚአብሔር አብራም የተባለውን ሰው ተናገረው። እግዚአብሔርም እንዲህ አለው አገርህንና ቤተ ሰብህን ትተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ። በዚያም እባርክሃለሁ፣ ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ ስምህንም ታላቅ አደርገዋለሁ፣ የሚባርኩህን እባርካለሁ፣ የሚረግሙህንም እረግማለሁ ባንተ ምክንያትም የምድር ሰዎች ሁሉ ይባረካሉ።

OBS Image

አብራምም እግዚአብሔርን ታዘዘ ሚስቱን ሦራንና አገልጋዮቹን ሁሉና ንብረቱንም ሁሉ ይዞ እግዚአብሔር ወዳሳየው የከነዓን ምድር ሄደ።

OBS Image

አብራም ከነዓን በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር “በዙሪያህ ያለውን ሁሉ ተመልከት የምታየውን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘሮችህ ውርስ አድርጌ እሰጣችኋለሁ” አለው። አብራምም በምድር ተቀመጠ።

OBS Image

ከዕለታት አንድ ቀን አብራም መልከ ጼዴቅ የተባለውን ታላቁን የእግዚአብሔር ሊቀ ካህናት ተገናኘው። መልከ ጻዴቅም አብራምን ባረከው እንዲህም አለው “የሰማይና የምድር ጌታ ታላቁ እግዚአብሔር አብራምን ይባርክ” አብራምም ለመልከ ጼዴቅ ካለው ሁሉ አሥራት ሰጠው።

OBS Image

ብዙ ዓመታት ቢያልፉም አብራምና ሦራ አሁንም ያለ ልጅ ይኖሩ ነበር። እግዚአብሔር ለአብራም እንደ ገና ተስፋ ሰጠው ልጅ እንደሚኖረውና ዘሮቹ እንደ ሰማይ ክዋክብት እንደሚበዙ ተናገረው። አብራምም በእግዚአብሔር ተስፋ አመነ። አብራምም በእግዚአብሔር ተስፋ በማመኑ ምክንያት ጻድቅ ሆኖ ተቈጠረ።

OBS Image

እግዚአብሔርምከአብራም ጋር ቃልኪዳን አደረገ። ቃልኪዳን በሁለት ወገኖች መካከል የሚደረግ ስምምነት ነው። እግዚአብሔርም አብራምን“ከገዛ አብራክህ ልጅእሰጥሃለሁ” አለው።“ለዘሮችህም የከነዓንን ምድር እሰጣለሁ።” አብራምግን በዚያን ጊዜ ያለ ልጅ ነበር።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘፍጥረት 11-15