am_obs/content/03.md

6.9 KiB

3. የጥፋት ውሃ

OBS Image

ከረጅም ጊዜ በኋላ ብዙ ሕዝቦች በዓለም ይኖሩ ነበር። እነርሱም በጣም ክፉዎችና ኃይለኞች ሆኑ። ክፋትም በጣም እየበዛ በመምጣቱ እግዚአብሔር ዓለምን ሁሉ በሚያጥለቀልቅ የጥፋት ውሃ አጠፋለሁ ሲል ወሰነ።

OBS Image

ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስን አገኘ። ኖኅ በዘመኑ ከነበሩት ሰዎች ሁሉይልቅ ጻድቅና ከበደል የራቀ ሰው ነበር።እግዚአብሔርም ሊልክ ስላቀደው የጥፋት ውሃለኖኅ ነገረው። ኖኅ ግዙፍ መርከብ እንዲሠራ እግዚአብሔርነገረው።

OBS Image

እግዚአብሔርም ለኖኅ መርከብ እንዲሠራ ነገረው። የመርከቢቱም ርዝመት 140 ሜትር ወርዷ 23 ሜትር ከፍታዋ 13.5 ሜትር ይሁን አለ። ኖኅ የሚሠራት መርከብ ከእንጨት የተሠራች ሆና ባለ ሦስት ፎቅ፤ ብዙ ክፍሎች ጣራና መስኮት ያሉአት ነበረች፤ መርከቢቱም ኖኅንና ቤተ ሰቡን፣ ሁሉንም ዓይነት የምድር ላይ እንስሳት ከጥፋት ውሃ እንድትጠብቅ ነገረው።

OBS Image

ኖኅም እግዚአብሔርን በመታዘዘ እግዚአብሔር እንደ ነገራቸውም ኖኅና ሦስቱ ልጆቹ መርከቢቱን ሠሩ። መርከቧ በጣም ትልቅ ነበረችና ሲሠራ ብዙ ዓመታት ፈጀ። ኖኅ ስለሚመጣው የጥፋት ውሃ ለሕዝቡ እያስጠነቀቀ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ ይነግራቸው ነበር ይሁን እንጂ አላመኑትም።

OBS Image

እግዚአብሔር ኖኅንና ቤተ ሰቡን በቂ ምግብ ለራሳቸውና ለእንስሳቱ እንዲያከማቹ አዘዘ ሁሉም ነገር ዝግጁ በሆነ ጊዜ ወደ መርከቢቱ ለመግባት ለኖኅ፣ ለሚስቱ፣ ለሦስቱ ወንዶች ልጆቹና ለሚስቶቻቸው ጊዜው መድረሱን ነገረው። ስምንት ሰዎችም ወደ መርከቢቱ ገቡ።

OBS Image

እግዚአብሔር ከጥፋት ውሃው እንዲጠበቁ የሁሉንም ተባእትና እንስት እንስሳት ወፎችን ጨምሮ ወደ ኖኅ ላከ። ለመሥዋዕት የሚያገለግሉ ሰባት ተባእትና ሰባት እንስት ከሁሉም ዓይነት እንስሳ ወደ ኖኅ መርከብ ላካቸው። ሁሉም ወደ መርከቡ እንደ ገቡ እግዚአብሔር ራሱ የመርከቡን በር ዘጋ።

OBS Image

ከዚያም ዝናቡ መዝነብ ጀመረ፣ ዘነበ፣ ዘነበ፣ ዘነበ ያለማቋረጥ ለ40 ቀንና ሌሊት ዘነበ፣ ከምድርም ምንጭ ይፈልቅ ነበር። በመላው ዓለም ያለው ሁሉም ነገር በውሃ ተሸፈነ፤ ረጃጅም ተራሮች እንኳ ሳይቀሩ በውሃ ተሸፈኑ።

OBS Image

በመርከቡ ከነበሩት ሰዎችና እንስሳት በቀር በምድር ይኖር የነበረ ነገር ሁሉ ሞተ፤ መርከቢቱም በውሃው ላይ ተንሳፍፋ በውስጧ የሚገኙትን ነፍሳት ሁሉ ከሞት አዳነች (አተረፈች)።

OBS Image

ዝናቡ መዝነቡን ካቆመ በኋላ መርከቢቱ ለአምስት ወራት ያህል በውሃው ላይ ተነሳፈፈች። በዚህም ጊዜ ውሃው መቀነስ ጀመረ። ከዕለታት አንድ ቀን መርከቢቱ በተራራው አናት ላይ አረፈች፤ ይሁን እንጂ ዓለም አሁንም በውሃ ተሸፍና ነበር። ከሦስት ወራት በኋላ የተራራ ጫፎች መታየት ጀመሩ።

OBS Image

ከአርባ ቀናት በኋላ ኖኅ ውሃው ከምድር ላይ ደርቆ እንደ ሆነ እንዲያይ ቁራ የተባለን ወፍ/አሞራ ላከ። ቁራው እዚህም እዚያም እየበረረ ደረቅ መሬት ቢፈልግም ሊያገኝ አልቻለም።

OBS Image

በኋላም ኖኅ ርግብ የተባለች ወፍ ላከ። ይሁን እንጂ የምታርፍበት መሬት ማግኘት ስላልቻለች ወደ ኖኅ ተመልሳ መጣች። ከሳምንት በኋላ ኖኅ እንደ ገና ርግቧን ላካት። እርሷም የወይራ ቅጠል በአፏ ይዛ ተመለሰች ውሃው ይቀንስ ስለ ነበር ተክሎችም ደግሞ መብቀል ጀመሩ።

OBS Image

ኖኅ ሌላ አንድ ሳምንት ጠብቆ ርግቢቷን ለሦስተኛ ጊዜ ሰደዳት፤ በዚህ ጊዜ የምታርፍበት ስፍራ ስላገኘች ተመልሳ አልመጣችም። ውሃው ይደርቅ ነበር።

OBS Image

ከሁለት ወራት በኋላ እግዚአብሔር ኖኅን አንተ ቤተ ሰብህና እንስሳቱ በሙሉ ከመርከቧ ውጡ አለው። ቤተ ሰቡ ከመርከቢቱ ወጡ። ብዙ ልጆችና የልጅ ልጆችን ወለዱ ምድርንም ሞሉአት።

OBS Image

ኖኅም ከመርከቢቱ ከወጣ በኋላ መሠዊያ ሠራና ከእያንዳንዱ እንስሳ ለመሥዋዕት ሊቀርቡ የሚችሉትን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረበ። እግዚአብሔርም በመሥዋዕቱ ተደሰተ ኖኅንና ቤተ ሰቡን ባረካቸው።

OBS Image

እግዚአብሔርም አለ። “ሰዎች ስለሚያደርጉት ክፉ ነገር ዳግም ምድርን ፈጽሞ ላልረግማት ቃል እገባለሁ። ምንም እንኳ ሰዎች ከልጅነታቸው ጀምሮ ኃጢአተኞች ቢሆኑም ዓለምን ዳግመኛ በጥፋት ውሃ አላጠፋም” አለ።

OBS Image

እግዚአብሔር ለቃል ኪዳኑ ምልክት ይሆን ዘንድ የመጀመሪያውን ቀስተ ደመና ሠራ። ሁልጊዜ ቀስተ ደመናው በሰማይ ላይ ይታያል። እግዚአብሔር በዚህ ቀስተ ደመና አማካይነት ለሕዝቡ የገባውን ኪዳን ያሳታውሳል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘፍጥረት 6-8